top of page

የጠቅላላ አባላት ስብስባ ጥሪ/ General Assembly Meeting



በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሐሚልተን መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ስለ ቤተ ክርስቲያኑ መተዳደሪያ ደንብ ለመነጋገር ልዩ የጠቅላላ አባላት ስብስባ እሁድ, መስከረም 20 2016 ዓ.ም (ኦክቶበር 1,2023) ከቅዳሴ ሥነ ሥርዓት በኋላ ያካሂዳል።


የስብሰባው ዓላማ በመንግሥት ማሳሰቢያ መሰረት የቤተክርስቲያኒቱ ህጋዊ ሰነድ እንዲመዘገብ ተወያይተን ለማፅድቅ እና በዚሁ ሰነድም መሰረት የመተዳደሪያ ደንቡ የተወሰኑ አንቀጾች እንዲሻሽሉ ስላስፈለገ ይህንኑ ተነጋግረን ውሳኔ እንድናስተላልፍ ነው።


ስለሆነም የቤተ ክርስቲያኑ አባል የሆናችሁ በሙሉ ከላይ በተጠቀሰው ቀን በቤተ ክርስቲያን ተገኝታችሁ ስብሰባው ላይ እንድትሳተፉና የአባልነት ግዴታችሁን እንድትወጡ በቤተ ክርስቲያናችን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።


የቤተ ክርስቲያኑ ሰበካ ጉባኤ

_______________________________________________________________________


Holy Trinity Ethiopian Orthodox Tewahedo Church’s Board invites all active members of the church to the special general assembly meeting that will be held on Sunday, October 1, 2023 at the church after mass services.


The purpose of the meeting is to discuss the corporation’s by-law. As per Canada’s non-profit act, we are required to submit an article of amendment and review the by-law accordingly. The purpose of the meeting is to review the amendments and provide approval.


All active members of the corporation are expected to attend the meeting to participate in the discussion and fulfil their obligation as members of the church.


HTEOTC Board


Comments


bottom of page