Starting June 14, 2020, the church will be open and resumes it regular mass and other services (see below for message in English)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
በሐሚልተንና አካባቢው ለምትገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ
የሐሚልተን ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በዓለም ዙሪያ በተከሰትው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት መንግስት ባወጣው እገዳ መሠረት ቤተ ክርስቲያናችን ለምእመናን ዝግ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።
በአሁኑ ሰዓት መንግስት ጥሎት የነበረውን እገዳ በተወሰነ ደረጃ ያሻሻለ ስለሆነ ከሚቀጥለው እሁድ ሰኔ 7 ቀን 2012 ዓ.ም (June 14, 2020) ጀምሮ ቤተ ክርስቲያናችን ለምእመናን ክፍት ሆኖ መንፈሳዊ አገልግሎቱን ይቀጥላል።
ስለዚህ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለማስቀደስ ስትመጡ:-
የጤና ባለሙያዎች በሚሰጡት መመሪያ መሠረት የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ፣
በየጊዜው በተሰጠው መመሪያ መሠረት ርቀትን መጠበቅ፣
የጉንፋንና የሳል ምልክት ከተሰማችሁ በቤት ሆናችሁ ጤናችሁን መከታትል፣
ልጆች ላልተወሰነ ጊዜ በቤታቸው እንዲቆዩ ቢደረግ፤ ይዛችኋቸው ከመጣችሁ ግን ወላጆች ሙሉ ኀላፊነት ወስዳችሁ ከአጠገባችሁ አንዳይለዩ በማድረግ በጥንቃቄ መጠበቅ አለባችሁ፣
ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምልክት በተደረገበት ቦታ ብቻ በመቆም/ በመቀመጥ/ ማስቀደስ አለባችሁ፣
ከቅዳሴ በኋላ ርቀታችሁን እንደጠበቃችሁ ቅዳሴ ጸበል እየጠጣችሁ ለጊዜው ምድርቤት/ቤዝመት/ ያለው ፕሮግራም ስለማይኖር ወደየቤታችሁ እንድትሄዱ በአክብሮት እናሳስባለን።
“ልዑል እግዚያብሔር በምህረትና በይቅረታ ይጎብኘን”
የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት
In light of the government announcement of June 8, 2020 regarding the re-opening of places of worship, the Holy Trinity Ethiopian Orthodox Tewahedo Church will open its doors and re-start mass services staring Sunday, June 14, 2020.
When you come to church for mass, please follow the following directions:
Wear face mask to prevent spread of disease as per public health directives
Maintain 2 metres of physical distance between congregants
If you are experiencing the most common symptoms of COVID-19 (cough, fever, shortness of breath, runny nose, or sore throat), it is better if you stay home and take care of your health
We recommend that kids stay home at this time. However, if you decide to bring your kids to church, you have to keep them with you during your stay for mass. There will be no access to the basement area.
During your stay at church, please sit/stand only at the designated areas maintaining your distance with others.
After mass, you can take holy water and leave in a queue maintaining distance. At this time, the after mass program in the basement will not take place.
HTEOTC Board of Directors
Comments